የግላዊነት ፖሊሲ

የዴንቬር (Denver) ቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብር የእኛን ድኅረገጽ ለሚጎበኙት የግል መብታቸው በተመለከተ በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ያደርግበታል። ምን መረጃ እንደሚንወስድ እና ያም መረጃ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እና በጥንቃቄ እንደሚጠበቅ ለማሳወቅ ይህን የግል መብት የመጠበቅ መምሪያ አዘጋጅተናል።

ይህን ድኅረገጽ በመጠቀም (https://dpp.org)፣ በዚህ ለተገለጹ ደንቦች እና ሁኔታዎች ዕውቅና ሰጥተዋል። ይህን መመሪያ በራሳችን ጊዜ እና ምንም ማሳሰቢያ መስጠት ሳያስፈልገን የመለወጥ መብት አለን።

የሚሰበሰበው መረጃ ምንድ ነው፣ ለምን?

ተጠቃሚው የእኛን ድኅረገጽ በሚጎበኝበት ጊዜ፣ የተጠቃሚውን ግለሰብ ማንነት ሳንገልጽ ስለተደረገው ጉብኝት መረጃ እንወስዳለን። ተጠቃሚው ከምን ቦታ ላይ እንደሚጎበኝ እና ተጠቃሚው ከምን ዓይነት ብራውዘር እየጎበኘ እንደሆነ የመረጃውን መስመር እንከታተላለን። ተጠቃሚው በእኛ ድኅረገጽ ላይ ስለሚያሳልፍበት ክፍለ ጊዜ ግልጽ የሆነ መረጃ እንወስዳለን። ይህም ቀን እና የጎበኘበት ሰዓት እና የተመለከታቸውን ገጾችን ያካትታል።

አንዳንድ ጊዜ ተጠቃሚው በፈቃደኝነት የግል ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ (PII) እንዲሰጠን እንጠይቀዋለን። ይህ መረጃ በአጠቃላይ የሚያካትተው፣ ነገር ግን በዚህ ብቻ የማይገደበው፣ ስምን፣ የኢሜይል አድራሻን፣ የፖስታ አድራሻን፣ እና የስልክ ቁጥርን ይሆናል። ተጠቃሚው ከሚከተሉት ነገሮች ውስጥ አንዱን በሚጠይቅበት ጊዜ ይህን መረጃ እንጠይቀዋለን፡

  • በኢንቴርኔት ቀጥታ መስመር ላይ ስብሰባን ወይም ገለጻን ለመከታተል በሚመዘገብበት ጊዜ
  • አንዳንድ የተወሰኑ መረጃዎችን ማለትም ነጭ ወረቀት ወይም የኮድ ናሙና ከእኛ በሚጠይበት ጊዜ
  • በፖስታ እንዲላክለት በዝርዝሩ ላይ በሚመዘገብበት ጊዜ
  • ከእኛ ጋር ለመስማማት
  • ወይም ማንኛውንም እኛ አስፈላጊ ነው ብለን ላመነው ለሌላ ተግባር

የዴንቬር (Denver) ቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብር ማንኛውንም የግል የገንዘብ ሁኔታ ወይም ከጤና ጋር የተያያዙትን የሚገልጽ የግል መረጃ አይወስድም። ዕሜያቸው ከ13 ዓመት በታች ከሆኑት ልጆች እያወቅን መረጃ አንወስድም።

መረጃው እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል?

ድኅረገጻችን እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ለማጤን እና ድኅረገጹ ይዘት እና የሚሰጣቸውን አገልግሎት ለማሻሻል እንዲያስችለን የግል ማንነትን የማይገልጽ መረጃን (non-PII) እንወስዳለን።

የድኅረገጹን ይዘት እና ለተጠቃሚው የሚሰጣቸውን አገልግሎት ለማሻሻል የግል ማንነትን የሚገልጽ መረጃ ይወሰዳል።

የዴንቬር (Denver) ቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብር የተወሰዱ መረጃዎችን በራሱ ጋር የሚያቆይ ሲሆን መረጃውን አይሸጥም፣ አይነግድበትም፣ ወይም ለሌሎች አያከራይም። መረጃውን ተጠቃሚውን ለማግኘት ልንጠቀምበት እንችላለን። ይህም ለክትትል የስልክ ጥሪ ማድረግ፣ ኢሜይል መላክ፣ ወይም መገኛው ላይ ክትትል ለማድረግ በፖስታ መልእክት መላላክ፣ ወይም ስለ ማስታወቂያዎች፣ አዳዲስ አገልግሎቶች፣ ወይም አስፈላጊ ስለሆነው የድኅረገጽ ላይ ለውጦችን በተመለከተ የገበያ መረጃ ለመስጠትን ሊያካትት ይችላል። የዴንቬር (Denver) ቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብር ይህን መረጃ ለተወሰነ የማስታወቂያ ወይም ለሚሰጠው የአገልግሎት ማስታወቂያ ዓላማ ከሥራ አጋሮቹ ጋር ሊጋራ ይችላል።

በድኅረገጹ ላይ “Cookies” ጥቅም ላይ ይውላሉ?

“Cookies” በድኅረገጹ ተጠቃሚው የመጠቀሚያ ዕቃ ላይ የሚገኙ ትንንሽ መረጃዎች ናቸው። የተሻለ አገልግሎት ልንሰጥዎት cookies ልንጠቀም እንችላለን። Cookies መዝገብ ለመያዝ ዓላማ ድኅረገጽ ወደ እርስዎ ኮምፒውተር የሚያስተላልፋቸው ጥቃቅን መረጃዎች ናቸው። Cookies ለተወሰነ ድኅረገጽ የእርስዎን ምርጫዎች የሆኑ መረጃዎችን በማቆየት ድኅረገጹን ይበልጥ ጠቃሚ ሊያደርጉ ይችላሉ። የ cookies ጥቅም ኢንዱስትሪው የሚሰራው መመዘኛ ሲሆን፣ አብዛኛው ዋና ዋና የሚባሉ ድኅረገጾች ለደንበኞቻቸው ጠቃሚ የሆነ አማራጮችን ለመስጠት ይጠቀሟቸዋል። የሚገቡት Cookies ምንም እንኳን የተጠቃሚዎችን ኮምፒውተር የሚለዩ ቢሆንም፣ በራሳቸው የተጠቃሚዎችን ማንነት አይለዩም። አብዛኛው ማሰሺያዎች ከጅምሩ cookies ለመቀበል የተሰሩ ናቸው። ከፈለጉ፣ የcookies ላለመቀበል ከፈለጉ የራስዎን ማሰሺያ መስራት ይችላሉ። ሆኖም ግን፣ ያን ካደረጉ የዴንቬር (Denver) የቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብርን ድኅረገጽ ሙሉ በሙሉ የመስራት ዕድሉን ማግኘት አይችሉም።

የግለሰብን ማንነት የሚገልጹ መረጃዎች እንዴት በጥንቃቄ ይጠበቃሉ?

የዴንቬር (Denver) የቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብር በኢንዱስትሪ የተቀመጡትን የመመዘኛ ስልቶች እና የአስራሪ ስልት ማለትም የኤሌክትሮኒክ መረጃዎችን ለመከላከል firewalls, intrusion monitoring, እና passwords ን ይጠቀማል። በርካታ የሆኑ የአካላዊ ደህንነት መጠበቂያ ስልቶች የመቆለፊያ ዕቃዎች እና የ24 ሰዓት የህንጻ መቆጣጠሪያ ተገጥሞላቸዋል። በመጨረሻም፣ ማንነትን የሚያሳውቅ መረጃን ለማግኘት የሚችሉት የግድ የማወቅ ሁኔታ ሲፈጠር ተወሰኑ ሰራተኞች የተገደበ ነው።

ከሌላ ድህረገጽ ጋር የተያያዙ Links

የዴንቬር (Denver) ቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብር ድኅረገጽ ከሌላ የኢንተርኔ ድኅረገጾች ጋር የተያይዙ links ሊኖሩት ይችላሉ። የዴንቬር (Denver) ቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብር ከውጪ የሆኑትን ድኅረገጾችን የማይቆጣጠራቸ ደግሞም የማይደግፋቸው ሲሆን ከእንደዚህ ዓይነት ድኅረገጾች ለሚገኙት መረጃዎች ተጠያቂም አይሆንም። ይህ መምሪያ የግል መብት መጠበቅ መመሪያዎችን እና የዴንቬር (Denver) የቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብር ያሉትን ድኅረገጾች የሚያደርጉትን የመረጃ አወሳሰድንም የሚሸፍን አይደለም።

ደብዳቤዎች እንዴት መርጦ ማውጣት ይቻላል

ተጠቃሚው የሰጠውን መረጃ መሰረት በማድረግ፣ የዴንቬር (Denver) የቅድመ ትምህርት ቤት መርኃግብር ለተጠቃሚው በመልእክት መላኪያ ኢሜይል ሊያደርግለት ይችላል። እያንዳንዱ መልእክት ተጨማሪ መልእክት ለመላክ ለምርጫ ቀላል የሆነ መንገድ አለው።