ከዴንቨር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ፕሮግራም በሚሰጥ የግል ትምህርት ብድር አማካኝነት በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ወጪ ላይ ገንዘብ ይቆጥቡ

በዴንቨር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ፕሮግራም ለመሳተፍ ፍላጎት ስላሳዩ እናመሰግናለን!

የ Denver Preschool Program (DPP) /ዴንቨር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ፕሮግራም/ ሁሉም በዴንቨር ከተማ እና ካውንቲ ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ላይ ገንዘብ እንዲቆጥቡ የሚያግዝ የአገር ውስጥ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት ነው። ምስጋና ለዴንቨር መራጮች ይሁን እና

የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ወጪዎች ላይ በየወሩ ምን ያክል ገንዘብ መቆጠብ ይችላሉ?*

የእርስዎን DPP የግል ትምህርት ብድር ይገምቱ

$

*ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የእርስዎን ሊያገኙ የሚችሉት የግል ትምህርት ብድር ለማየት የግል ትምህርቱን ዝርዝሮች ያስገቡ።

$0
/ወር

እንዴት መጀመር ይችላሉ?

1 –የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ይምረጡ

የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት እስካሁን ካላገኙ ፍለጋዎን እዚህ ላይ መጀመር ይችላሉ፦ https://find.dpp.org/welcome/

ወይም የቅድመ ትምህርት ቤት ናቪጌተርን በ enroll@dpp.org ያግኙ ወይም በ 303-595-4377 ቅድመ ትምህርት ቤት ለማግኘት እርዳታ ያግኙን።

2-ለ DPP የግል ትምህርት ብድሮች የእርስዎ ማመልከቻ ያስገቡ

የእርስዎን ማመልከቻ ይጀምሩ

ለግል ትምህርት ብድሮች ብቁ ለመሆን፣ የእርስዎ ልጅ የሚከተሉትን ማሟላት አለበት፦

  • በዴንቨር ከተማ እና ካውንቲ ውስጥ ነዋሪ መሆን
  • እርስዎ ለሚያመለክቱበት የትምህርት ዘመን ከኦክቶበር 1 በፊት ዕድሜው 4 የሚሆን
  • የ DPP-ተሳትፎ ፕሮግራም ውስጥ መሳተፍ

ማመልከቻዎችን በደብዳቤ፣ በፋክስ ወይም በአካል በመቅረብ ማስገባት የሚመርጡ ከሆነ የ PDF ማመልከቻውን ለማውረድ እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ.

ስለ ዴንቨር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት /Denver Preschool Program (DPP)/ የበለጠ ይወቁ

ስለ ዴንቨር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት /Denver Preschool Program (DPP)/ የበለጠ ይወቁ

ስለ ዴንቨር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ፕሮግራም፣ ስለ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የግል ትምህርት ብድሮች እና እንዴት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤትን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል የበለጠ ለማወቅ ከዚህ በታች ያሉትን ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች ያንብቡ። ተጨማሪ ጥያቄዎች ካልዎት ወይም ስለ DPP የበለጠ ለማወቅ ከሆነ ሰው ጋር ለመነጋገር የሚፈልጉ ከሆነ ለእኛ በ info@dpp.org ላይ ኢሜይል ይጻፉልን ወይም ወደ 303.595.4377 ይደውሉ።

DPP የግል ትምህርት ብድሮችን በተመለከተ ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

አንድ ልጅ ሲመዘገብ ወይም ስትመዘገብ DPP የልጁን ወይም የቤተሰቡን የኢሚግሬሽን ሁኔታ ይጠይቃል?

አይጠይቅም። የዴንቨር ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ፕሮግራም ተማሪዎችን የኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ከግምት ሳይገባ እና በዘር፣ በብሔር፣ በቀለም፣ በብሔራዊ ምንጭ ወይም ሃይማኖት ላይ ምንም ዓይነት መድልዎ ሳያደርግ ይመዘግባል።

የ DPP ማመልከቻ ለመሙላት ምን ማድረግ አለብኝ?

የ DPP ማመልከቻን ለመሙላት፣ የሚከተሉትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርብዎታል፦ 1) የእርስዎ ልጅ ዕድሜ 2) የእርስዎ በዴንቨር ከተማ እና ካውንቲ ውስጥ ያለው የአሁን አድራሻ እና 3) ወርኃዊ ገቢ።

DPP የሚከተሉን ይቀበላል፦

  • የእርስዎ ልጅ የልደት ምስክር ወረቀት፣ የጥምቀት ምስክር ወረቀት፣ የፍርድ ቤት ማኅደር፣ የክትባት ካርድ ወይም የእርስዎን ልጅ ዕድሜ ለማረጋገጥ የሚረዳ ቀን ያለበት የሆስፒታል ማስረጃ ቅጂ።
  • የሊዝ፣ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም አገልግሎት የተሰጠበትን አድራሻ እና ለእርስዎ አድራሻ ማረጋገጫ እንዲሆን የወላጅ/አሳዳጊ ስም የሚያሳይ እንደ የጋዝ፣ የመብራት ወይም የውሃ ክፍያ የመሳሰለ የወርኃዊ ፍጆታ ደረሰኝ።
  • ለእያንዳንዱ በእርስዎ ቤተሰብ ውስጥ ያለ ወላጅ/ሞግዚት የገቢ ማረጋገጫ እንዲሆን ቢያንስ የአራት ተከታታይ ሳምንታትን ገቢ የሚያሳዩ ማረጋገጫ ሰነዶች።

በተጨማሪ የአንዳንዱን የሚያስፈልጉ ሰነዶች ቃለ መሃላ ሰነድ እንቀበላለን። ቃለ መሃላ መስጠት የሚፈልጉ ከሆነ ወይም እኛ ለማገዝ ማድረግ ያለብን ማናቸውም ነገር ካለ፣ ለእኛ በስልክ ቁጥር 303.595.4377 ይደውሉልን ወይም ኢሜይል በ info@dpp.org ይላኩልን።

ስለ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ልጄን ለምን በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ማስገባት ይኖርብኛል?

ለበርካታ ዐሠርት ዓመታት የተደረጉ ጥናቶች ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በመደበኛ ትምህርት ቤት ስኬታማነትን ሊያበረታታ ይችላል፣ የተሻለ የሥራ ዕድልን ያስገኛል፣ ሌላው ሳይቀር ወንጀልን ይከላከላል። በትምህርት ቤት ስኬታማ ላለመሆን ከፍተኛ ስጋት ላለባቸው ልጆች የሚሰጡት ጥቅማ ጥቅሞች ተለቅ ያሉ ሲሆኑ፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ጥቅማ ጥቅሞች ለሁሉም ልጆች የገንዘብ አቅማቸው ምን እንደሆነ ከግምት ሳይገባ ይሰጣቸዋል።

የጥራት ደረጃ አሰጣጥ ምን ማለት ነው?

የኮሎራዶ ሻይንስ የጥራት ደረጃ አሰጣጥ እና ማሻሻያ ሥርዓት /Colorado Shines Quality Rating & Improvement System (QRIS)/ ለአገልግሎት አቅራቢዎች ጥራትን ማሻሻል የሚያስችል ዘዴን ይፈጥራል። ፈቃድ ያላቸው የሕፃናት እንክብክቤ እና የአፍላ ዕድሜ ትምህርት አገልግሎት አቅራቢዎች በአምስት መስኮች ይመዘናሉ፣ በመቀጠል 5 ምርጡ ሆኖ ከ1 እስከ 5 የሚሰጥ ድምር ነጥብ ያገኛሉ። ይህ ውጤት አፍላ ዕድሜ ትምህርት እና የትምህርት አገልግሎት አቅራቢዎች ከየት ተነሥተው በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ላይ ልጆችን እና ቤተሰቦቻቸውን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚችሉ የሚያሳይ መሠረትን ይጥላል።

በመቀጠል ምን እንደሚያደርጉ እርግጠኛ አይደሉም?

የዴንቨር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤትን /Denver Preschool Program/ ያነጋግሩ

በአቅራቢያዎ ወዳለ ከፍተኛ ጥራት ያለው የቅድመ ትምህርት ቤት እንዲያገኙ እና መክፈል እንዲችሉ ለማገዝ እኛ አለንልዎት። ስለ ዴንቨር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ጥያቄዎች ካልዎት፣ ወይም ለግል ትምህርት ድጋፍ ለመመዝገብ እገዛ ለማግኘት፣ ከዚህ በታች ያለውን መረጃ በመጠቀም ይደውሉ።

የግል ትምህርት ብድር ጥያቄዎች

ስልክ፦ 303.595.4DPP(377)
ኢሜይል፦ info@dpp.org

የግል ትምህርት ብድር ማመልከቻዎችን ያስገቡ

መሥመር ላይ (ኦንላይን)፦ https://dpp.org/start-your-application/
በኢሜይል፦ info@dpp.org
በፋክስ፦ 303.295.1750
በደብዳቤ፦
Denver Preschool Program
P.O. Box 40037
Denver, CO 80204-0037

ለቤተሰቦች ተጨማሪ መረጃዎች፦

  • ወደ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ዕድሜ ላልደረሰ ልጅ በዴንቨር ውስጥ የልጅ መዋያ ተቋም ማግኘት ይፈልጋሉ? ወደ 2-1-1- ይደውሉ እና ከ United Way ጋር ይነጋገሩ፣ የልጅ እንክብካቤ ግብዓት እና መላኪያ አገልግሎትን ይሰጣል።
  • ከዴንቨር ውጭ የልጅ መዋያ ተቋም ወይም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ማግኘት ይፈልጋሉ? ሊገኙ የሚችሉ የልጅ እንክብካቤ ፕሮግራሞች በስቴቱ ውስጥ ያሉ ሙሉ ዝርዝርን ለማግኘት Colorado Shines ን ያነጋግሩ ወይም ወደ 1-877-388-2273 ይደውሉ።

*አንድ ቤተሰብ የሚቀበለው የገንዘብ ድጋፍ መጠን በቤተሰብ መጠን እና ገቢ፣ የተመረጠው የቅድመ መደበኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጥራት እና ልጁ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቱ በሚቆይበት ልክ የሚወሰን ነው። ከላይ ያለው ግምት እርስዎ ባስገቡዋቸው መስኮች ላይ የተመረኮዘ ነው እና የትምህርት ቤቱ ደረጃ 4 ነው። የእርስዎ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት እስካሁን የ DPP የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤ አጋር ካልሆነ፣ እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ እንዲያውቁ እኛን እንዲያነጋግሩ እባክዎ ያበረታቷቸው።